በወንዶች ማራቶን የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድሩን መጨረስ አልቻሉም

You are currently viewing በወንዶች ማራቶን የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድሩን መጨረስ አልቻሉም

AMN-መስከረም 04/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳልያ የጠበቀችበት የወንዶች ማራቶን ላይ የተወዳደሩ አትሌቶች ውድድሩን መጨረስ አልቻሉም።

ለሊት በተደረገ የወንዶች ማራቶን ደሬሳ ገለታ ፣ ታደሰ ታከለ እና ተስፋዬ ድሪባ ኢትዮጵያን ወክለዋል።

ከስድስት ወር በፊት የቶክዮ ማራቶንን አሸንፎ የዓመቱን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበው ታደሰ ታከለ 34ኛው ፣ ደሬሳ ገለታ ደግሞ 35ኛው ኪሎ ሜትር ላይ አቋርጠዋል።

ተስፋዬ ድሪባም ወድድሩን ሳያጋምስ ለማቋረጥ ተገዷል።

ውድድሩን ታንዛኒያዊው አልፎንስ ፍሊክስ ሲምቡ አሸንፏል። ሲምቡ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለታንዛኒያ ወርቅ ያመጣ የመጀመሪያው አትሌት ሆኗል።

በኤርትራ የተወለደው ጀርመናዊው አማኑኤል ጴጥሮስ ከሲምቡ ጋር እስከ መጨረሻው ተፎካክሮ ሁለተኛ ወጥቷል።

ጣልያናዊው ኢሊያስ ኦዋኒ ለሀገሩ የነሃስ ሜዳልያ አስገኝቷል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review