የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በህዳሴ ግድብ ግንባታ ውስጥ ያሳዩትን ትጋት በቀጣይ በሌሎች ስራዎች ሊደግሙት ይገባል ሲሉ አርቲስቶች ገለጹ

You are currently viewing የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በህዳሴ ግድብ ግንባታ ውስጥ ያሳዩትን ትጋት በቀጣይ በሌሎች ስራዎች ሊደግሙት ይገባል ሲሉ አርቲስቶች ገለጹ

AMN – መስከረም 4/2018 ዓ.ም

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በህዳሴ ግድብ ግንባታ ውስጥ ቁጭትን ከመፍጠር ግድቡ እስኪጠናቀቅ ያሳዩትን ትጋት በቀጣይ በሌሎች ስራዎች ሊደግሙት ይገባል ሲሉ አርቲስቶች ገልጸዋል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን መቋጨትን አስመልክቶ የቁንጅና ውድድርና የኪነ ጥበብ መድረክ ተካሒዷል።

በመድረኩ የተገኙት የኪነ ጥብብ ባለሙያዎች ይህ ትውልድ በህብረት ቆሞ ያሳካውን ድል የማስረጽ ተግባር ከዘርፉ ይጠበቃል ብለዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያዊያንን በአንድነት ያሰባሰበ ዳግማዊ አደዋ ነው ያሉት ባላሙያዎቹ፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በሙያቸው በህዝብ ዘንድ ቁጭትን ከመፍጠር ጀምሮ የግድብ ግንባታውን እስከ ማስተበበርና ህዝብን እስከ ማጀገን ድረስ ያሳዩትን ትጋት በቀጣይ የህዝብን አንድት በማጽናት ትውልዱን ለቀጣይ ድል ማዘጋጀት ይገባል ብለዋል።

አርቲስቶቹ በተዘጋጀው መድረክ ስለ አባይ ወንዝና ህዳሴ ግድብ የሰሯቸውን ስራዎች አቅርበዋል።

በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review