በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለተገኘው ውጤት ቀጣይነት ሁላም ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ
የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ አስገንዝበዋል፡፡
የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት መጀመርን ተከትሎ የደጃዝማች ወንድይራድ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የትምህርት ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ፤ እንደ ከተማ በ2017 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አበረታች ውጤት መመዝገቡን አስታውሰዋል።
የደጃዝማች ወንድይራድ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተማሪዎች ምገባና የትምህርት ቁሳቁስ ማቅረብን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራትን በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል።
በ2017 የትምህርት ዘመን 99 በመቶ የስድስተኛና ስምንተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎቹን ስለማሳለፉ የሚገልፀው ትምህርት ቤቱ፤ በተያዘው የ2018 የትምህርት ዘመን ሁሉንም ተማሪዎቹን የማሳለፍ ውጥን መያዙን ገልጿል።
ለተጀመረው የመማር ማስተማር ዘመን ውጤታማነት ከትምህርት ማህበረሰቡ ባሻገር ወላጆችን ጨምሮ ሁሉም የድርሻውን ሃላፊነት እንዲወጣ ተጠይቋል።
በመቅደስ ደምስ