የብላክ ላየን ሰርከስ ቡድን የሆነው ትሩፕ አዲስ አበባ በሩሲያ አገር በተካሄደው የሰርከስ ኒውክሊን / Nikulin Circus Moscow/ እጅግ ድንቅ በሆነ አቀራረብና ፉክክር የብር መዳሊያ አሸናፊ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ቡድኑ ባለፈው አመት በፈረንሳይ በተካሄዱት የአለማችንን አንጋፋው ሰርከስ ፌስቲቫል ሰርከስ ሞንቴካርሎ/Cirque Monte Carlo/ ላይ የነሃስ አንዲም በቦርዴክ አለም አቀፍ ፌስቲቫል/11th Cirque de Bayeux,France/ ላይ የወርቅ ዋንጫ አሸናፊ መሆን የቻለ ድንቅ የሰርከስ ቡድን መሆኑ ተገልጿል፡፡
አባላቱ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርከስ ፕሬዝዳንት አርቲስት ተክሉ አሻግርና የአዲስ አበባ ሰርከስ ማህበር ም/ፕሬዝዳንት አርቲስት ቢኒያም እንዳለ አቀባበል አድርገዉላቸዋል፡፡
በአንተነህ አለማየሁ