ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቀኝ ግዛት ትርክትን በኃይል ለመጫን የተደረገን ጥረት የሰበረ የዚህ ትውልድ ዳግማዊ አድዋ ነው ሲሉ አቶ አወሉ አብዲ ገለጹ

You are currently viewing ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቀኝ ግዛት ትርክትን በኃይል ለመጫን የተደረገን ጥረት የሰበረ የዚህ ትውልድ ዳግማዊ አድዋ ነው ሲሉ አቶ አወሉ አብዲ ገለጹ

AMN – መስከረም 7/2018 ዓ.ም

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ በመላው ኦሮሚያ የድጋፍ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ እየተካሔደ ባለው የድጋፍ ሰልፍ ላይ መልእክት ያስረላለፉት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ አወሉ አብዲ እንደገለጹት፣ የህዳሴ ግድብ እውን መሆን ከኢኮኖሚ ጠቀሜታው ባሻገር በሐገራችን ላይ በኃይል ለመጫን የታሰበውን የቅኝ ግዛት ትርክት የተሰበረበት የዚህ ትውልድ ዳግማዊ አድዋ ነው ብለዋል።

ይህ ትውልድ ታሪክ አውሪ ብቻ ሳይሆን የራሱን ታሪክ መጻፍ ችሏል ያሉት አቶ አወሉ፣ ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተባትን ሁሉን አቀፍ ጦርነት ተቋቁማ ታላላቅ ድሎችን ማስመዝገብ እንደምትችል አሳይቷል ብለዋል። የኢትዮጵያዊያንን የዘመናት ቁጭት የመለሰ ስለመሆኑም አቶ አወሉ አብዲ ገልጸዋ፡፡

በሄኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review