ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ስብራት መፍትሔው መደመር ብቻ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ስብራት መፍትሔው መደመር ብቻ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ
  • Post category:ፖለቲካ

‎AMN – መስከረም 7/2018 ዓ.ም

‎ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ስብራት መፍትሔው መድመር ብቻ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት የመደመር መንግስሥት መፅሐፍ ተመርቆ ለንባብ በበቃበት ወቅት ነው።

‎የመደመር መንግሥት በዋናነት ኢትዮጵያውያንን በጋራ ራዕይ ላይ መሰብሰብ ያስፈልጋል ብሎ እንደሚያምን አስረድተው፤ በጋራ ራዕይ ከተሰባሰቡ በኋላ ስብራት በመለየት፤ መፍትሔ በማበጀት ላይ እንደሚያተኩርም ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ የእድገት ጉዞ እና የፖለቲካ ስብራት ዋነኛው ማነቆ “የጠላቶቻችን አጀንዳ” መሆኑን ጠቅሰዋል።

‎ይህንን ሲያብራሩ በዘር፣ በሀይማኖት፣ በፆታ ፣ በሰፈር እና በመንደር ባልተገባ መንገድ መለያየት ትልቁ የፖለቲካ ስብራት መሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚህ ስብራትን የሚጠግነው መደመር ነው ሲሉ መፍትሔውን አስቀምጠዋል። እኛ መደመር ስንል ጠላቶቻችን ይደነግጣሉ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ስንደመር ስለምንሰራው ታሪክ የጥንት ታሪካችን ማሳያ ነው ብለዋል።

‎ኢትዮጵያውያን ዘር ሳንጠቅስ በጋራ መቆም ብንችል መፍጠን እና መፍጠር እንችላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአስፈላጊ ቦታ ደግሞ ከ መከተል ወደ መዝለል ፣ ከተቀባይነት እና ከተከታይነት መላቀቅ እንችላለን ብለዋል። መከፋፈል የኛ የኢትዮጵያውያን ሀሳብ አይለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጫና የተደረገበት እሳቤ ለመከላከል እንደመራለን ብለዋል።

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review