አዲስ አበባ ከተማ በጥቂት ዓመታት ያመጣችው ለውጥ በድፍን አፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing አዲስ አበባ ከተማ በጥቂት ዓመታት ያመጣችው ለውጥ በድፍን አፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

AMN – መስከረም 07/ 2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ በጥቂት ዓመታት ያመጣችው ለውጥ በድፍን አፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

በመደመር መንግሥት መፅሃፍ መረቃ ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በአዲስ አበባ ከተማ የተሰራው የለውጥ ስራ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

በራስ አቅም እና በራስ ገንዘብ፤ ባጠረ ጊዜ ከመቆሸሽ እና ከመጨለም ልምምድ በመውጣት ለዜጎች ምቹ ከተማ አድርጎ መስራት እንደሚቻል በተግባር የታየበት ስራ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ይህም በጥቂት አመታት በድፍን አፍሪካ ምሳሌ የሚደረግ ተግባር ነው ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

የመንግስት መፈክር ከቢሮ እስከ ከተማ፣ ከከተማ እስከ ሃገር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አሁን ላይ ከዚህ አልፈን በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመሩ ከተማን የማልማት እና የመቀየር ስራዎች፣ በበርካታ የሃገራችን አካባቢ እና ከተሞች በሚያስደንቅ ሁኔታ በመተግበሩ፣ ከተሞቹ በሚያስደንቅ ፍጥነት እየተለወጡ መሆናቸውን ነው የገለፁት፡፡

በሰራነው ጥቂት ስራ በመጣ ለውጥ ከተመፃደቅን አናድግም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በቁጭታችን ልክ በመትጋት የጀመርነውንም ስራ ሳይቆራረጥ በማስቀጠል ድፍን ኢትዮጵያን የውበት፣ የለውጥ እና የዘመናዊነት ምሳሌ ማድረግ ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review