‎በሚቀጥሉት አስር ቀናት አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የክረምቱ ዝናብ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ

You are currently viewing ‎በሚቀጥሉት አስር ቀናት አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የክረምቱ ዝናብ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ
  • Post category:ወክታዊ

AMN – መስከረም 7/2018 ዓ.ም

በሚቀጥሉት አስር ቀናት አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የክረምቱ ዝናብ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቷ አካባቢዎች መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖራቸው የ2017/18 ዓ.ም ትንበያ ማመላከቱን በኢንስቲትዩቱ የትንበያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል፡፡

ይህ የተከሰተውም በተለይም ከደቡባዊ የህንድ ውቅያኖስ በመነሳት ወደ ኢትዮጵያ ሲነፍስ የነበረው እርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ ከእለት ወደ እለት እየተስፋፋና እየተጠናከረ በመምጣቱ መሆኑንም ነው ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ 464 በሚደርሱ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ እጅግ ከባድ መጠን ያለው የዝናብ መጠን መመዝገቡንም አንስተዋል፡፡

በቀጣዮቹ አስር ቀናትም እስከ 250 ሚሊ ሜትር የሚደርስ ዝናብ እንደሚስተዋል ያነሱት አሳምነው (ዶ/ር)፤ ከዕለት ወደ እለት ወደ አርብቶ አደሩ እና ከፊል አርብቶ አደሩ የዝናብ ስርጭቱ እንደሚስፋፋ አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ተናግረዋል፡፡

በእነዚህ ቀናት አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለይም በምዕራብ ሸዋ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በሰሜን ምዕራብ እንዲሁም በአዋሽ ተፋሰስ አካባቢዎች ላይ ዝናቡ ቀጣይነት ስለሚኖረው ማህበረሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

በአይናለም አባይነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review