ሊቨርፑል ፣ ባየርን ሙኒክ እና ፓሪሰን ዠርማ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድራቸውን በድል ጀምረዋል

You are currently viewing ሊቨርፑል ፣ ባየርን ሙኒክ እና ፓሪሰን ዠርማ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድራቸውን በድል ጀምረዋል

AMN-መስከረም 07/2018 ዓ.ም

በሜዳው አንፊልድ አትሌቲኮ ማድሪድን ያስተናገደው ሊቨርፑል 3ለ2 አሸንፏል።

አሌክሳንደር ኢዛክ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀዩ መለያ በታየበት ጨዋታ የማሸነፊያ ግቦቹን አንዲ ሮበርትሰን ፣ ሞሐመድ ሳላህ እና ቨርጅል ቫንዳይክ አስቆጥረዋል። የስፔኑን ክለብ ሁለት ግቦች ማርከስ ዮሬንቴ ከመረብ አሳርፏል።

በሌሎች ጨዋታዎች ባየርን ሙኒክ ቼልሲን 3ለ1 ረቷል። ለጀርመኑ ክለብ ሀሪ ኬን በፍፁም ቅጣት ምት እና በጨዋታ ሁለት ግብ ሲያስቆጥር ትሬቮህ ቻሎባህ በራሱ ላይ ሌላኛውን ግብ ማስቆጠር ችሏል። የቼልሲን ብቸኛ ግብ ኮል ፓልመር አስቆጥሯል። በሜዳው አታላንታን ያስተናገደው ፓሪሰን ዠርማ በማርኪንሆስ ፣ ኪቪቻ ክቫራስኬሊያ ፣ ኑኖ ሜንዴዝ እና ጎንካሎ ራሞስ ግቦች 4ለ0 አሸንፏል።

ኢንተር ሚላን ከሜዳው ውጪ ከአያክስ ጋር ተጫውቶ የ 2ለ0 ድል አግኝቷል። ፈረንሳዊው አጥቂ ማርከስ ቱራም ሁለቱንም ግቦች በስሙ አስመዝግቧል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review