የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ በደመቀ ስነ ስርዓት እንዲከበር ሁሉም የድርሻውን ማበርከት እንዳለበት የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጿል፡፡
ቢሮው ያዘጋጀው የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል አከባበር ዝግጅትን በማስመልከት በቢሾፍቱ የፖናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል የባህል ተሃድሶን በሚያረጋግጥ ሁኔታ እንዲከበር የክልሉ መንግስት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ጀሚላ ስንብሩ ተናግረዋል፡፡
በዓሉ ህዝብ ለህዝብ ለማቀራረብ ያለውን ሚና እና የቱሪዝም ፋይዳውን በመገንዘብ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም የቢሮ ሀላፊዋ ገልጸዋል።
በፓናል ውይይቱም የኢሬቻ እሴቶችና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ፣ ለባህልና ለሠላም እንዲሁም ለቱሪዝም ዘርፉ እድገት እያበረከተ ያለውን አስታዋጽኦ በተመለከተ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎችም ቀርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

በውይይቱም አዲሱ ትውልድ ኢሬቻ ባህላዊ ወግና ትውፊቱን ጠብቆ እንዲከበር ሚናውን መወጣት እንዳለበት ተመላክቷል።
ለዚህም ከመንግስትና ከአባገዳዎችም በርካታ ድጋፎች እንደሚጠበቁም ተገልጿል።
በአለሙ ኢላላ