የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ጋር ሊወያዩ ነው፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩናይትድ ኪንግደም 2ኛውን ጉብኝታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ፕሬዝዳንቱ በንጉስ ቻርለስ 3ኛ እና ንግስት ካሚላ ንጉሳዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ይህንንም ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ በጉብኝታቸው 2ኛ ቀን ከሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡
ውይይታቸው ከፖለቲካዊ ጉዳዮች ይልቅ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር ሮይተርስ አስነብቧል፡፡
በቅርቡ አሜሪካ በብሪታኒያ የ150 ቢሊዮን ዩሮ ወይም 205 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ለማድረግ መስማማታቸውም ተዘግቧል፡፡
ቴክኖሎጂ፣ የሃይል እና ሌሎችንም ጉዳዮች የሚያካትተው የኢንቨስትመንት ስምምነቱ ሃገራቱ ልዩ የሆነ ግንኙነት እንዲኖራቸው የሚያስችል እንደሆነ ታምኖበታል፡፡
ኬር ስታርመር፤ ትራምፕ ስልጣን ከያዙ ጀምሮ ቴክሎጂን የማልማት ፅኑ ፍላጎት እንደነበራቸውን ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበርም በዘገባው ተካቷል፡፡
በሊያት ካሳሁን