ኢትዮጵያ በ2025 የዓለም አቀፍ የሕዝብ ደኅንነት ኢንዴክስ እና ሪፖርት ላይ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቧ ተገለፀ

You are currently viewing ኢትዮጵያ በ2025 የዓለም አቀፍ የሕዝብ ደኅንነት ኢንዴክስ እና ሪፖርት ላይ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቧ ተገለፀ

AMN – መስከረም 8/2018 ዓ.ም

የ2025 የዓለም አቀፍ የሕዝብ ደኅንነት ኢንዴክስ እና ሪፖርት ላይ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሕዝብ ደኅንነት ጥበቃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቧን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራው ልዑካን ቡድን በቻይና ጂያንግሱ ግዛት በዓለም አቀፍ የሕዝብ ደህንነት ትብብር ፎረም ዓመታዊ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

በዚህ ጉባኤ ላይ ከ130 ሀገራት በላይ የተውጣጡ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የፖሊስ አዛዦች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር “አንድ ዓለም የጋራ ደኅንነት” የሚለው የትብብር መሪ ቃል ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊነቱ የጎላ መሆኑን መግለፃቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የሀገራትን ቅንጅታዊ ትብብር ሚና በአፅንኦት አንስተው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሪፎርም ውጤቶችንም ማጋራታቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ኮሚሽነር ጀነራል አባል የሆኑበት የትብብሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በስብሰባውም ላይ የ2025 የዓለም አቀፍ የሕዝብ ደኅንነት ኢንዴክስ እና ሪፖርት ይፋ ሆነዋል፡፡

ይፋ በሆኑት ኢንዴክስ እና ሪፖርት ላይ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሕዝብ ደኅንነት ጥበቃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቧ ተመላክቷል።

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የሕዝብ ደህንነት ትብብር ፎረም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆና ንቁ ተሳትፎ እያደረገች ሲሆን በዚህም የኢትዮጵያ አጠቃላይ ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ከፍ ወዳለ ደረጃ መድረሱ ተገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review