ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በቀጠናው ያለንን ተሰሚነት ያሳደገ ዘመን ተሻጋሪ የስኬት ማህተም ያረፈበት ፕሮጀክት ነው ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ተናገሩ

You are currently viewing ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በቀጠናው ያለንን ተሰሚነት ያሳደገ ዘመን ተሻጋሪ የስኬት ማህተም ያረፈበት ፕሮጀክት ነው ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ተናገሩ
  • Post category:ልማት

AMN መስከረም 9/2018

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ መመረቁን በማስመልከት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እና በተለያዩ የክልሉ ከተሞች የድጋፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በጅግጅጋ እየተካሄደ ባለው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ባስተላለፉት መልዕክት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁሉንም ያስተሳሰረና አንድነትን ያጠናከረ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።

የግድቡ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠበት እለት አንስቶ በተላይም የውሃ ሙሌት ከተጀመረ በኋላ በርካታ ፈተናዎች ያጋጠሙት ፕሮጀክት መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ፈተናዎቹና ጫናዎቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቆራጥ አመራርና በኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ ከዳር መድረሱን አውስተዋል።

ግድቡ የትውልድ አሻራ ያረፈበት የህብረታችን ማሳያ መሆኑን ያነሱት አቶ ሙስጠፌ፤ ግድቡ ዘመን ተሻጋሪ የልማት ስኬት ነው ብለዋል።

እንደ ርዕሰ መስተዳደሩ ገለጻ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዘመን ተሻጋሪ የስኬታችን ማህተም ያረፈበት ፕሮጀክት ነው ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከዚህም ባለፈ የግድቡ መጠናቀቅ በቀጣይ መንግስት የወጠናቸው ተላላቅ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማሳካት ትልቅ መነሳሳትን የፈጠረ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም የሶማሌ ክልል ፕሮጀክቶቹ ከሚከናወኑባቸው አካባቢዎች አንዱ በመሆኑ ህዝቡ ትኩረቱን ልማት ላይ ማድረግ አለበት ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review