አሜሪካ የጸጥታው ምክር ቤት የጋዛ ተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳብን ለ6ተኛ ጊዜ ተቃወመች

You are currently viewing አሜሪካ የጸጥታው ምክር ቤት የጋዛ ተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳብን ለ6ተኛ ጊዜ ተቃወመች

AMN:-መስከረም O9/2018 ዓ.ም

አሜሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቀውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ውድቅ አድርጋለች።

ዋሽንገተን ምክር ቤቱ በጋዛ አስቸኳይ ዘላቂ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾች እንዲለቀቁ የሚጠይቀውን የውሳኔ ሀሳብ ነው ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን በመጠቀም የሻረችው።

በምክር ቤቱ የመካከለኛው ምስራቅ ምክትል የአሜሪካ ተወካይ ሞርጋን ኦርታገስ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡ የእስራኤልን ራስን የመከላከል መብት እና ለሃማስ አስከፊ ድርጊት በቂ እውቅና አልሰጠም ብለዋል።

ቀሪ 14 ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት እስራኤል የእርዳታ ቁሶች እንዳይገቡ ያደረገችውን ክልከላ እንድታቆም እና ቋሚ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቀውን የውሳኔ ሀሳብ ደግፈውታል።

ከድምጽ አሰጣጡ በኋላ የምክር ቤቱ አባላት የአሜሪካን ውሳኔ በጽኑ አውግዘውታል። የፍልስጤም አምባሳደር ሪያድ መንሱር “ምክር ቤቱ ትክክለኛ ሚናውን እንዳይወጣ የተጋረጠ እንቅፋት” ብለውታል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ቢሮ እስራኤል በቅርቡ የጀመረችውን አዲስ ዘመቻ ተከትሎ ወደ ጋዝ እርዳታ የሚገባበት ብቸኛ መስመር ለአደጋ ተጋልጧል ብሏል።

ውሳኔው የተላለፈው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በመሪዎች ደረጃ የሚያደርገው አጠቃላይ ጉባኤ ሊካሄድ ቀናት ሲቀሩት ነው

በዳዊት በሪሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review