የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዱባይ ከሚገኘው ዳሊል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጋር

You are currently viewing የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዱባይ ከሚገኘው ዳሊል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጋር

ለወንጀል መከላከል፣ ለወንጀል ምርመራ እና ለኢንተለጀንስ አገልግሎት የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን በጋራ ማበልጸግ የሚያስችለዉን የውል ስምምነት ተፈራረመ

AMN መስከረም 10/ 2018

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዱባይ ከሚገኘው ዳሊል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ/ Dalil Information Technology/ ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችለዉን የውል ስምምነት በዋናው መሥሪያ ቤት ተፈራርሟል።

ስምምነቱ ለወንጀል መከላከል፣ ለወንጀል ምርመራ እና ለኢንተለጀንስ አገልግሎት የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን በጋራ ለማበልጸግ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ዙሪያ አብሮ ለመሥራት የሚያግዝ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አምባሳደር መሐመድ ሰላም አህመድ አል-ረሺድ በተገኙበት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ነብዩ ዳኜ ከዳሊል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ካምፓኒ የኮሙዩኒኬሽን ዋና ኦፊሰር ሚስተር ታላል አል-አህመድ ጋር የውል ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

አምባሳደር መሐመድ ሰላም አህመድ አል-ረሺድ እና የካምፓኒው ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሪፎርሙ የታጠቃቸውን የቴክኖሎጂ አቅሞችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸዉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review