ከንቲባ አዳነች አቤቤ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ያስገነቧቸዉን 1 ሺህ 671 ያህል ቤቶች ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማስተላለፋቸዉን ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ያስገነባናቸውን 1 ሺህ 671 ያህል ቤቶች ለአገር ባለውለታዎች ፣ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለከፋ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ እና በወንዝ ዳርቻዎች ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አስረክበናል ብለዋል።
የቤት ግንባታዎቹ አብሮነትን እና ጉርብትናን የሚያጠናክሩ፣ የህፃናት መጫዎችን ፣ የስፓርት ማዘዉተሪዎችን የያዙ፣ በአጠቃላይ ንፁህና ሰው ልጅ የሚገባውን የከበረ የአኗኗር ዘይቤ የሚያዳብሩ ናቸው።

ይህን በጎ ተግባር በእውቀታቸው፣ በሃብታቸው፣ በጉልበታቸው የደገፉ ልበ ቀና ባለሀብቶችን እና ያስተባበሩ አመራሮቻችንን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉ ገልጸዋል።