የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በይቻላል መንፈስና በአብሮነት ያሳኩት ፕሮጀክት መሆኑን የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር አስታወቁ።
በሀረሪ ክልል የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መጠናቀቅና መመረቅን ምክንያት በማድረግ የማስ ስፖርት ተካሂዷል።
በመርሃግብሩ ላይ የክልሉ ምክትል ርእስ መስተዳድር ሮዛ ኡመር፣ የብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
እንዲሁም ወጣቶች የስፖርት ቤተሰቦች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር በወቅቱ እንዳሉት፤ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በይቻላል መንፈስና በአብሮነት ያሳኩበት ፕሮጀክት ነው።
የክልሉ ህዝብም ግድቡ እውን እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋዕኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።
በሕዳሴ ግድብ የተመዘገበው ስኬት ለሌሎች ስኬቶችም መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን አመልክተው፤ በቀጣይ ለሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ከፍ ያለ እሳቤን የፈጠረ ነው ብለዋል።
በአካል ብቃት እንቅስቃሴው የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎችም በሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የአንድነት ምልክት መሆኑን ተናግረዋል።