አዲስ አበባ ከተማን የማዘመን እና ለነዋሪዎች ዘመናዊ አኗኗርን እዉን የማድረጉ ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ጃንጥራር አባይ ገለፁ

You are currently viewing አዲስ አበባ ከተማን የማዘመን እና ለነዋሪዎች ዘመናዊ አኗኗርን እዉን የማድረጉ ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ጃንጥራር አባይ ገለፁ

‎AMN መስከረም 11/2018 ዓ.ም

‎አዲስ አበባ ከተማን የማዘመን እና ለነዋሪዎች ዘመናዊ አኗኗርን እዉን የማድረጉ ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለፁ፡

‎ሀላፊው ይህንን የተናገሩት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞችበሰጡበት ወቅት ነው።

‎አቶ ጃንጥራር ባለፋት የለዉጥ አመታት በ24/7 የስራ ትጋት የአዲስ አበባን ገፅታ መቀየር የዜጎችንም አኗኗር ማሻሻል ብለዋል

‎መዲናዋን የማዘመን ለነዋራዎቿ ምቹ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡

‎የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ምስክር ነጋሽ በበኩላቸው፣ በክፍለ ከተማዉ ለአቅመ ደካሞች የሚተላለፉ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች በስፋት እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

‎ ዛሬ ለነዋሪዎች የተላለፈዉ ባለ ሦስት ወለል መኖሪያ ቤትም ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የተገነባ መሆኑን አመላክተዋል ፡፡

‎በክፍለ ከተማዉ ልማትን ከዜጎች ተጠቃማነት ጋር በማስተሳሰር በዉጤት የታጀቡ ስራዎች እየተሰሩ ነዉም ብለዋል፡፡

‎በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review