የመደመር መንግሥት መፅሀፍ የዘመናት ችግሮችን የዳሰሰ እና መፍትሄ አመላካች መሆኑን በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ምሁራን ገልፀዋል።
የመደመር መንግሥት መፅሃፍ እሳቤ ላይ ያተኮረ ውይይት በየካ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል። የመደመር መንግሥት እሳቤ በተለያዩ ምሁራን ግንዛቤን የሚፉጥሩ የተለያዩ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን ሰፊ ውይይትም ተደርጓባቸዋል።
የውይይቱ አላማ የመደመር መንግሥት ዕሳቤን በማህበረሰቡ ለማስረጽ መሆኑን የተናገሩት የየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መገርሳ ገላና፤ በቀጣይም ተመሳሳይ መርሃ ግብሮች በክፍለ ከተማው ይቀጥላሉ ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎቹ የመደመር መንግሥት መፅሀፍ ለቀጣይ ትውልድ መሠረት የሚጥል እና ሀገርን በጋራ ለማሻገር የሚያግዝ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል።
የመደመር መንግሥት መፅሀፍ ፍጥነትና ፈጠራን እንዲሁም ክፍተቶችን የማረም አቅም የሚፈጥር መሆኑም በመድረኩ ተመላክቷል።
በመርሃ ግብሩ የተለያዩ ምሁራን፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ ፖለቲከኞችና ማህበረሰብ አንቂዎች እንዲሁም በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ምሁራን ተሳትፈዋል።
በመሀመድኑር ዓሊ