ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በይፋ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠታቸውን አስታወቁ

You are currently viewing ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በይፋ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠታቸውን አስታወቁ

AMN – መስከረም 11/2018 ዓ.ም.‎

ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በይፋ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠታቸውን አስታውቀዋል።

ውሳኔውን ተከትሎ ለፍልስጤም ሀገርነት እውቅና የሰጡ ሀገራትን ቁጥር ከ140 በላይ እንዲሻገር አድርጎታል።

ለሁለት ዓመታት እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄደችው ያለው ወታደራዊ ዘመቻን ተከትሎ በርካታ ህገራት ለፍልስጤም የህገርነት ዕውቅናን እየሰጡ ነው።

የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ሞሀሙድ አባስ እውቅና ለስጡ ሀገራት ምስጋናቸውን ገልጸው ውሳኔው እስራኤል እና ፍልስጤም በሰላማዊ ጉርብትና እንዲኖሩ የሚያስችል ነው ብለዋል።

እስራኤል በበኩሏ ይህ በምዕራባውያን ሀገራት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ሐማስ ለፈጸመባት ጥቃት እንደ ሽልማት የሚቆጠር ነው በሚል በጽኑ እንዳወገዘችው ቢቢሲ ዘግቧል።

የሁለት ሀገርነት መፍትሄ የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት የሚደገፍ ቢሆንም በእስራኤል ዘንድ ግን ተቀባይነት አላገኝም።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review