ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ የድሬደዋ ነዋሪዎች ደስታቸውን በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየገለፁ ነው።
ከማለዳ ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የአስተዳደሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።
የድጋፍ ሰልፈኞቹ “ግድቡ የኔ ነው፣ በህዳሴ ግድቡ የጀመርነውን ጉዞ በሌሎች ፕሮጀክቶች ላይ እንደግመዋለን፣ አባይ በአገሩ ለልማትና ለብልፅግና ውሏል፣ በህብረት ችለናል፣ ግድባችን ተጠናቋል የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችንም በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
በዋና ዋና ጎዳናዎች የድጋፍ ድምፃቸውን ያሰሙት ነዋሪዎች በአሁኑ ሰዓት በድሬደዋ ስታዲየም በጋራ በመሆን መልዕክታቸውን ማሰማታቸውን ቀጥለዋል።
በሰልፍ ስነስርዓቱ ላይ ከነዋሪዎች በተጨማሪ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ መሆናቸዉን ተዘግቧል።