የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በአላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴታቸዉን ጠብቀዉ እንዲከበሩ የድርሻቸዉን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ እና የሸገር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

You are currently viewing የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በአላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴታቸዉን ጠብቀዉ እንዲከበሩ የድርሻቸዉን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ እና የሸገር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

AMN መስከረም 13/2018

የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በአላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴታቸዉን ጠብቀዉ እንዲከበሩ አስፈላጊዉን ዝግጅት ማድረጋቸዉን የየካ ክፍለ ከተማና በሸገር ከተማ አስተዳደር የመነ አቢቹ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

የየካ ክፍለ ከተማና በሸገር ከተማ አስተዳደር የመነ አቢቹ ክፍለ ከተማ አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መጪዎቹን የአደባባይ በአላት በስኬት ማስከበር በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል፡፡

በአላቱ እሴታቸውንና ትውፊታቸውን ጠብቀው ሐገረዊ ገጽታን ከፍ በሚያደርግ አኳሃን እንዲከበሩ በጋራ መስራት እንደሚገባ በመድረኩ ተነስቷል።

በአላቱን የህዝቦች መስተጋብርን በማጠናከርና የኢትዮጵያውያንን ባህልና እሴት በሚያስተዋውቅ አግባብ ለማክበር በቅንጅት እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡

በአላቱ ሐይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች የሚንጸባረቁባቸዉ ከመሆናቸዉም በላይ የኢኮኖሚ መነቃቃትን የሚፍጥሩ በመሆናቸው ኢንተርፕራይዞችና የንግዱ ማህበረሰብ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ተጠቃሚ የሚሆንበት መደላድል እንደሚፈጥርም ተጠቁሟል፡፡

በአላቱ በስኬት እንዲጠናቀቁ ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ የሐይማኖት አባቶችና አባ ገዳዎች በሚሰጡት መመሪያ መሰረት ዝግጅቶችን በማስተባበርና በማሳለጥ የበኩላቸዉን ሊወጡ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

በሄኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review