የተባበሩት መንግሥታት አባል ሀገራት ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለች ዓለም ለመፍጠር በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ።
80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ በይፋ ተከፍቷል።
በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድንም በ80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው።
በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይም የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸውም፤ አባል ሀገራት ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለች ዓለም ለመፍጠር በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የተባበሩት መንግሥታትን ሥርዓትና መዋቅር ለ21ኛው ክፍለ ዘመን በሚመጥን ልክ መለወጥ እንደሚገባም በአጽንኦት ገልጸዋል።
የዓለም ኀብረተሰብ ምርጫውን ሠላም፣ ፍትሕ ዘላቂ ልማት እና ሰብዓዊ ክብር ሊያደርግ እንደሚገባ አስገንዝበው፤ ለተግባራዊነቱም ቁርጠኝነትን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል።