የደመራና የመስቀል በዓል ያለምንም አደጋ ክስተት እንዲከበር በአደጋ ቅንሳና በአደጋ ምላሽ ዘርፍ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ ንጋቱ ማሞ ለኤ ኤም ኤን እንደገለፁት፤ በአዲስ አበባ በተመረጡ ቦታዎች በተለያዩ አማራጮች የጥንቃቄ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡
ከዚህ አልፎ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች በአስራ አንዱም ቅርንጫፍና በማዕከል ያሉ የአደጋ ምላሽ ባለሞያዎችና ማሽነሪዎች እንዲሁም የአምቡላንስ አገልግሎቶች ክብረ በዓሉን ታሳቢ ያደረጉ ዝግጅቶች መደረጋቸውንም አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡
መላው የከተማው ነዋሪ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከኮሚሽኑ እየተላለፉ የሚገኙ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በመተግበር በዓሉ ያለ አደጋ ክስተት እንዲጠናቀቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ኮሚሽኑ ማሳሰቡን ገልፀዋል።
ህብረተሰቡ ለእሳት፣ ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥኖ እንዲያሳውውም አሳስበዋል፡፡