የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የመስቀል ደመራ በዓል በስኬት እንዲከናወን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት መሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የመስቀል ደመራ በዓል በስኬት እንዲከናወን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት መሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ

AMN – መስከረም 14/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመስቀል ደመራ በዓል በስኬት እንዲከናወን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት መሪዎች ጋር በዋና መስሪያ ቤት ውይይት አካሂዷል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከሃይማኖት መሪዎች ጋር በዚህ መልክ ተገናኝቶ መወያየቱ በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ያስችላል ብለዋል።

ኮሚሽነር ጀነራል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገራችን በቴክኖሎጂ የታገዘ በርካታ የፖሊስ ሠራዊት በማሰማራት ከክልልና ከፌደራል የፀጥታና አካላት ጋር በመቀናጀት አጠቃላይ የፀጥታ ማስከበር ሥራ እየተሰራ እንደሆነም መግለፃቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት መሪዎች የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርን በተመለከተ ከፀጥታና ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄዷቸው በርካታ የሕዝብ ንቅናቄ መድረኮች መላው ሕብረተሰብ የበዓሉ ባለቤት በመሆን በዓሉ በስኬት እንዲከበር ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን በውይይቱ ወቅት ገልፀዋል።

በዚህ ዓመት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ ባር ኮድ ያላቸው የመኪና ማለፊያ (car pass) እና የክብር እንግዶች የመግቢያ ባጆች መዘጋጀታቸውንም የሃይማኖት መሪዎች አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመላው ሀገራችን ስምሪት ወስዶ ውድ ሕይወቱን እየከፈለ በሀገራችን የተካሄዱ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረኮች ደህንነታቸው ተጠብቆ በስኬት እንዲጠናቀቁ ላደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ቤተ ክርስቲያኗ ትልቅ ክብር እንደምትሰጥ የሃይማኖት መሪዎች መናገራቸውንም በመረጃው ተገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review