የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላትን በጋራ በስኬት ማክበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረና ሴቶችን ያሳተፈ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላትን በጋራ በስኬት ማክበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረና ሴቶችን ያሳተፈ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

AMN – መስከረም 15/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማና የሸገር ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላትን በስኬት ማክበር በሚቻልበት ዙሪያ የሴቶች መድረክ እየተካሔደ ይገኛል፡፡

መስቀል ደመራና ኢሬቻ የሐገራችን ህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውንና ማህበራዊ መስተጋብራቸውን የሚያጠናክሩበት፣ የአንድነትና የፍቅር ተምሳሌት መሆኑን በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቆንጂት ደበላ ተናግረዋል።

በዓላቱ በተለይም ለሴቶች ልዩ ትርጉም አላቸው ያሉት ወ/ሮ ቆንጂት፣ ሴቶች ደምቀውና ተውበው ወደ አደባባይ በመውጣት የበዓላቱን ትውፊታዊ ይዘት ለዓለም ህዝብ ማስተዋወቅ ይገባል ብለዋል።

ከዚህም ባሻገር በአላቱ በስኬት እንዲጠናቀቁ ሴቶች አንድነታቸውን በማጎልበት የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ከሁለቱም ከተሞች የተወጣጡ ሴት የህብረተሰብ ክፍሎእና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በሄኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review