በክረምት በጎ ፍቃድ የሚሰሩ ሰው ተኮር ተግባራት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ከማቅለልም ባሻገር የአብሮነትን እሴቶችን የሚያጎለብቱ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ህይወት ሳሙኤል ገለፁ።
የአዲስ አበባ ከተማ የግንባታና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን በቂርቆስ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ባለሀብቱን በማስተባበር ከ1.2 ሚሊየን ብር በላይ የተገነባ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ማስረከብና አፍርሶ የመገንባት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል።

በክረምት በጎ ፍቃድ የሚሰሩ ሰው ተኮር ተግባራት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ከማቅለልም ባሻገር የአብሮነት እሴቶችን የሚያጎለብቱ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ህይወት ሳሙኤል ተናግረዋል።
የአቅመ ደካማ እንባዎች የሚታበስባት አዲስ አበባ ለበጎነት በተዘረጉ እና መስጠት እንደማያጎል በተረዱ ልጆቿ ዛሬም በርካታ ችግሮችን የሚያስተናግዱ ዜጎቿ ከችግራቸው ተላቀው ነገን እንዲናፍቁ ማድረግ ተችሏል ያሉት ኢንጂነር ህይወት ሳሙኤል፤ ይህ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ሰው ተኮር የሆኑ በጎ ተግባራት ክረምትን መሰረት አድርገው የሚተገበሩ ብቻ አለመሆናቸውን ያነሱት ዳይሬክተሯ፤ ይህ የክረምት ዘጠና ቀናት እቅድ አካል ነው ብለዋል።
የቤት እድሳት የተደረገላቸው አቅመ ደካማ ዜጎች ከዚህ በፊት የነበሩበት ቤት ለኑሮ የማይመች እንደነበር አስታውሰው ለተደረገላቸው የቤት እድሳት ምስጋና ችረዋል።
በመሀመድኑር አሊ