መሬትን ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ ነው

You are currently viewing መሬትን ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ ነው

AMN – መስከረም 15/2018 ዓ/ም

መሬትን ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ለተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ይበልጥ አቅም በመፍጠር በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ ማድረግ የሚያስችሉ አሰራሮችን ቀርፆ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አቶ መኮነን ያዒ ተናግረዋል።

ቢሮው የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ ማቋቋሚያ መድረክ እያካሄደ ነው፡፡ በዚሁ ጊዜ አቶ መኮነን እንዳሉት የመማክርት ጉባኤው መቋቋም ቀደም ሲል በቢሮው የተጀመሩ የሪፎር ስራዎችን ይበልጥ የሚያጠናክርና ተገልጋዩን የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል ድርሻ እንዲኖረው የሚያስችል ነው ብለዋል።

በከተማዋ የሚሰጡ መንግስታዊ አገልግሎቶች ቀልጣፋ፣ ፍትሓዊና ዘመናዊ እንዲሁም ከብልሹ አሰራር የፀዱ እንዲሆኑ የሚያስችሉ አሰራሮችን በየጊዜው ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው፤ የሚሰጡ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የተደገፉ መሆናቸው ለውጦችን ማስመዝገብ ተችሏል ነው ያሉት።

ሆኖም ግን አዳጊ ከሆነው የተገልጋይ ፍላጎት አንፃር አሁንም የሚነሱ ቅሬታዎችን ለማስቀረት ተገልጋዩን ያሳተፈ አሰራርና አደረጃጀት ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

መማክርቱ ከ20 እስከ 50 የሚሆኑ ያሉት ሲሆን በአባልነትም የሲቪክ ማሕበራት፣ ከተገልጋዩ ማሕበረሰብ፣ ከተቋሙ ጽ/ቤት እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ መሆኑ ተመላክቷል።

በታምሩ ደምሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review