በማዕድ ማጋራት ተግባር የተቸገሩትን የመርዳት እሴቶቻችንን እያዳበርንበት ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

You are currently viewing በማዕድ ማጋራት ተግባር የተቸገሩትን የመርዳት እሴቶቻችንን እያዳበርንበት ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

AMN – መስከረም 16/2018 ዓ.ም

በማዕድ ማጋራት ተግባር የቆየዉን የመደጋገፍ እና ተካፍሎ የመኖር ባህል ከሰዉ ተኮር እሳቤዎቻችን ጋር አቆራኝተን የተቸገሩትን የመርዳት እሴቶቻችንን እያዳበርንበት ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ በሁሉም ክፍለ ከተማዎች እና ወረዳዎች ዘውትር በዓል በመጣ ቁጥር እንደምናደርገው የመሰቀልና የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተናል ብለዋል።

በዚህ ተግባር የቆየዉን የመደጋገፍ እና ተካፍሎ የመኖር ባህል ከሰዉ ተኮር እሳቤዎቻችን ጋር አቆራኝተን የተቸገሩትን የመርዳት እሴቶቻችንን እያዳበርንበት ነዉ።

ይህንን የበጎ ፈቃድ ተግባር ከጎናችን ሆናችሁ የምትደግፉ ልበ ቀናዎች በሙሉ በተጠቃሚዎች ስም ምስጋናዬ ይድረሳችሁ በማለት አመስግነዋል።

ከንቲባዋ መልካም የመስቀል ደመራ በዓል በማለት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review