እንደ ደመራው ምሳሌ ተደምረን የኢትዮጵያን ጉስቁልና በመናድ ብልጽግናዋን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

You are currently viewing እንደ ደመራው ምሳሌ ተደምረን የኢትዮጵያን ጉስቁልና በመናድ ብልጽግናዋን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – መስከረም 16/2018 ዓ/ም

እንደ ደመራው ምሳሌ ተደምረን የኢትዮጵያን ጉስቁልና በመናድ ብልጽግናዋን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ኃይማኖታዊ ትውፊትና ሥርዓቱን ጠብቆ በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ በአደባባይ የሚከበሩ በአላት አንዱ የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል የብዝሀ አብሮነትን የሚያጠናክር በመሆኑ ለቀጣይ ትውልድ ይዘቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይገባል ብለዋል፡፡

የመስቀል በዓል ሲከበር ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠበት ቀንን የሚያስታውሰን ነው ያሉት ከንታባዋ፤ ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲስ ዘመን የምንሻገርበት ነውም ብለዋል፡፡

እንደ ደመራው ምሳሌ ተደምረን የኢትዮጵያን ጉስቁልና በመናድ ብልጽግናዋን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉም ከንቲባዋ ገልፀዋል፡፡

የአፍሪካ መልህቅ የሆነችው አዲስ አበባን ውበቷን በሚጨምር መልኩ በማደስ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ህብር፤ ለቱሪስቶች ደግሞ መስህብ ለማድረግ መቻሉንም ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡

መስቀል ከጨለማ ወደ ብርሃን የምንሸጋገርበት እንደሆነ ሁሉ፤ እንደ ሀገር የሀገራችን ጨለማ ለመግፈፍ ህዝቡ በጋራ በመረባረበብ የታላቁን ህዳሴ ግድብን የገነባንበት ወቅት በመሆኑ በዓሉን ከወትሮው ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በ-በረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review