የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ባህሉን በጠበቀና በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን የሸገር ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ገልፀዋል፡፡
የሸገር ከተማ አስተዳደር የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል በስኬት ማጠናቀቅ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተማ ከተማ ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
በውይይቱ የተገኙት የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር ተሾመ አዱኛ የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ህዝብን አንድነት፣ እና ብሔር ብሄረሰቦችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ ከተለያዩ ሀገራት ህዝቦች ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
ወጣቶች በሰላምና ልማት ላይ ያላቸው ሚና የጎላ በመሆኑ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በዓሉን በማስተዋወቅ እና እንግዶችን በመቀበል ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው በመድረኩ ተመላክቷል።
ኤ ኤም ኤን ያነጋገራቸው የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ባህሉን እና ስርዓቱን በጠበቀ መንገድ እንዲከበር የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልፀዋል።
በዓሉን በማስተዋወቅ እና እንግዶችን በመቀበል ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ማሳየት ከሁሉም እንደሚጠበቅም በመድረኩ ተመላክቷል።
በመሀመድኑር አሊ