የኢሬቻ በአል ውበቱን እና ድምቀቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም የመዲናዋ ነዋሪ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን አሳስበዋል፡፡
ኢሬቻ ለወንድማማችነት በሚል መሪ ቃል የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በየካ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል።
በመገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ በተካሄደው የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ፣ የክፍለ ከተማው አመራሮች፣ ወጣቶች ነዋሪዎች እና እንግዶች ተሳትፈዋል።
በአሉ የአንድነት የወንድማማችነት እና የአብሮነት እንደመሆኑ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ወጣቱ እና ነዋሪው የበኩሉን ሚና እንዲወጣ አቶ በላይ ደጀን ጥሪ አቅርበዋል።
ሆረ ፊንፊኔ መስከረም 24 በአዲስ አበባ፤ ሆረ አርሰዴ ደግሞ በቢሾፍቱ መስከረም 25 በድምቀት ይከበራሉ።
በሰለሞን በቀለ