መገናኛ ብዙሃን የኢሬቻን ባህላዊ እሴት በማስተዋወቅና በማስተማር ረገድ ያላቸዉን ሚናቸዉን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

You are currently viewing መገናኛ ብዙሃን የኢሬቻን ባህላዊ እሴት በማስተዋወቅና በማስተማር ረገድ ያላቸዉን ሚናቸዉን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

‎AMN መስከረም 19 ቀን 2018 ዓም

‎መገናኛ ብዙሃን የኢሬቻ በዓል አከባበር ባህላዊ እሴትን በማስተዋወቅና በማስተማር ረገድ ያላቸውን ሚና እንዲወጡ የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ወሮ ጀሚላ ሲንቢሩ ጥሪ አቀረቡ ።

የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በአል አከባበር በተመለከተ ከሃገር ውስጥ እና ከውጭ ሃገር የሚድያ ባለሞዎች ጋር በኦሮሞ ባህል ማዕከል ውይይት አካሄዷል፡፡ የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት ” በሚል መሪ ቃል የሚከበር ሲሆን፣ ይህም በዓሉ ኢትዮጰያ የምትገኝበትን የማንሰራራት ጉዞ የሚገልፅ ነው ሲሉ ሃላፊዋ ገልፀዋል ፡፡

‎የመገናኛ ብዙሃን በዓሉን ለማስተዋወቅ ላደረጉት አስተዋፅኦ አመስግነው፣ የኢሬቻ በዓልን በተመለከተ የተሳሳተ አመለካከትን የሚያራምዱ አንዳንድ አካላት ወደ ትክክለኛው እሳቤ እንዲመጡ ማስቻል ይገባል ብለዋል። ‎የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ በበኩላቸው፣ መገናኛ ብዙሀን ትክክለኛውን የኢሬቻ ባህላዊ እሴት በማስተዋወቅ የተሳሳቱ እሳቤዎችን ማረም እንደሚገባቸዉ አስገንዝበዋል።

‎ኢሬቻ ብሄር ብሄረሰቦችን ጨምሮ ከተለያዩ የዉጭ ሃገራት የሚመጡ ቱሪስቶች የሚታደሙበት በአል በመሆኑ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ እንዲከበር መገናኛ ብዙሀን የማስተማር ሚናቸውን እና ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ በአፅንኦት ተናግረዋል።

‎የኢሬቻ በዓል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ እንዲመዘገብ መገናኛ ብዙሃን ባህሉን የማስተዋወቅ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በሄለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review