የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አባል ነኝ በማለት ሰዎችን በማስፈራራት እያገተ ገንዘብ ሲቀበል የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ

You are currently viewing የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አባል ነኝ በማለት ሰዎችን በማስፈራራት እያገተ ገንዘብ ሲቀበል የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ

AMN – መስከረም 19/2018 ዓ.ም

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አባል ነኝ በማለት ሰዎችን በማስፈራራት እያገተ ገንዘብ ሲቀበል የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

ዳዊት ጥላሁን ወይም ምንተስኖት ጥላሁን የተባለው ግለሰብ ሀሰተኛ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መታወቂያ በመጠቀም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ ነኝ በማለት ሰዎችን በማገትና በማስፈራራት ገንዘብ እንደሚቀበል ከህብረተሰቡ የመጣን ጥቆማ መነሻ በማድረግ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በጥምረት ባደረጉት ክትትል ግለሰቡን መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም በቁጥጥር እንዲውል ማድረግ መቻላቸውን መምያ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ አስታውቋል።

ተጠርጣሪው ከሜክሲኮ ወደ ጋርመንት በታክሲ ተሳፍራ የምትሄድን የግል ተበዳይን ሳሮን ተስፋዬን ደህንነት ነኝ በማለት በማስፈራራት እና በመደብደብ ጉዳት ያደረሰባት መሆኑን የግል ተበዳይ በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨቷ ይታወቃል።

ግለሰቡ በግል ተበዳይ ላይ ባደረሰው ጉዳት በህግ የሚጠየቅ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል ።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት ሀሰተኛ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መታወቂያ እንደተገኘበት ተገልጿል፡፡

በግለሰቡ በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት የተፈጸመበት ግለሰብ እና ስለ ግለሰቡ ማንኛውም መረጃ ያለው ሰው ለአዲስ ለአበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መረጃ በመስጠት ትብብር እንዲያደረግ እና የጸጥታ አካላትና አባል ነን በማለት የሚያስፈራሩና ተጽዕኖ የሚያሳደሩ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት በወቅቱ ለፖሊስ እንዲያሳውቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review