የአብሮነት በዓል – ኢሬቻ

You are currently viewing የአብሮነት በዓል – ኢሬቻ

AMN – መስከረም 20 /2018 ዓ.ም

በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በታላቅ ድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የኢሬቻ በዓል አንዱ እና ዋነኛው ነው ።

በዓሉ የክረምትን መውጣት እና የፀደይ መምጣት ተከትሎ የሁሉ ፍጥረት የሆነው ፈጣሪ የሚመሰገንበት ወቅት ነው ኢሬቻ።

በበዓሉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የሚሳተፍ ሲሆን በአብሮነት በፍቅር እና በመተሳሳብ የሚከበርም ነው ። የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ዋና ፀሓፊ እና የቱለማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው እና የምስጋና በዓል መሆኑን ጠቅሰዋል ።

የክረምቱ ጭጋግ ተገፎ ደመናው ጠርቶ በወንዞች ሙላት የማይገናኙ ቤተሰቦች የሚገናኙበት ነው በዚህ ምክንያት ለፈጣሪያቸው ኢሬሳ ወይም ምስጋና የሚያቀርቡበት ወቅት መሆኑን አባ ገዳ ጎበና ተናግረዋል ።

ኢሬቻ ኢትዮጰያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጰዩውያንን የሚያስተሳስር በዓል መሆኑን የገለፁት አባገዳ ጎበና ሆላ ሁሉም ኢትዮጰያውን እና አጎራባች አባባቢዎች ጭምር የሚሳተፉበት እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል።

የኢትዮጰያ የብሄር ብሄረሰብ ህዝቦች በመቻቻል በመከባበር በመፈቃቀር የሚኖሩባት አገር መሆኗን የሚገልፁት አባ ገዳ ጎበና ይህ አብሮነት ከማህበራዊ መስተጋብር ባሻገር በትዳር እና በደም የተሳሰረ መሆኑን አስረድተዋል ።

የአንድነት እና የአብሮነት በዓል የሆነው የኢሬቻ በዓል በንፁህ ልብ እና በይቅርታ ልቦና የሚከወን መሆኑንም ነው አባ ገዳ ጎበና ሆላ የገለፁት ።

በርካታ ታዳሚያን የሚሳተፍበት የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ከአገር ውስጥ እና ከውጭ አገር የሚመጡ ዜጎች ጥሩ ግዜን እንዲያሳልፉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል ።

በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review