ሊቨርፑል ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ተሸነፈ

You are currently viewing ሊቨርፑል ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ተሸነፈ

AMN-መስከረም 21/2018 ዓ.ም

በፕሪምየር ሊጉ በክሪስታል ፓላስ የተሸነፈው ሊቨርፑል በቻምፒየንስ ሊጉም ተሸንፏል። ከሜዳው ውጪ ጋላታሳራይን የገጠመው ሊቨርፑል 1ለ0 ተረቷል።

የጨዋታውን ብቸኛ ግብ ናይጄሪያዊው አጥቂ ቪክቶር ኦሲምኸን በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል። የቀድሞ የናፖሊ ተጫዋች በቻምፒየንስ ሊግ ያስቆጠራቸውን ግቦች ብዛት 10 አድርሷል። እዚህ ቁጥር ላይ የደረሰ የመጀመሪያው ናይጄሪያዊ ሆኗል።

በጨዋታው ሊቨርፑል ግብ ጠባቂው አሊሰን ቤከር እና ሁጎ ኢኪቲኬን በጉዳት አጥቷል። ዋና ዳኛው ክሌሞን ተርፓን ለቀዮቹ ፍፁም ቅጣት ምት ሰጥተው ውሳኔያቸውን በቫር ቀልብሰዋል።

በቻምፒየንስ ሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን የተሸነፈው ሊቨርፑል በቀጣይ ፍራንክፈርትን ይገጥማል። በሌሎች ጨዋታዎች አትሌቲኮ ማድሪድ ፍራንክፈርትን 5ለ1 ሲያሸንፍ አንቷን ግሪዝማን 200ኛ ግቡን ለአትሌቲኮ አስቆጥሯል።

ኢንተር ሚላን ስላቪያ ፕራግን 3ለ0 ሲረታ ፣ ማርሴ አያክስን 4ለ0 አሸንፏል። ባየርን ሙኒክ ፓፎስን 5ለ1 ሲያሸንፍ ኒኮላስ ጃክሰን ለሙኒክ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል።

ጆዜ ሞሪንሆ ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ በተመለሱበት ጨዋታ ቼልሲ ቤኔፊካን 1ለ0 ማሸነፍ ችሏል። የኖርዌውን ክለብ ቦዶ የገጠመው ቶተንሃም 2ለ2 ተለያይቷል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review