የኢሬቻ በዓል በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በታላቅ ድምቀት ከሚከበሩ በዓላትና ከገዳ ስርዓት መገለጫዎች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህ ህዝባዊ በዓል እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል።

የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 24 የሚከበረውን ሆረ ፊንፊኔ በዓል የሚከበርበትን ኢሬቻ ፓርክ የማፅዳት ስራ ተካሂዷል።
በፅዳት ስራው ከአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ አመራሮች፣ አርቲስቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ሆራ ፊንፊኔን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ መካሄዱን ገልፀዋል።

የኢሬቻ ፓርክን የማስዋብና ፅዳቱን የመጠበቅ ስራ በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሲሰራ መቆየቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ገዛኸኝ ዴሲሳ ተናግረዋል።
የዘንድሮ ሆረ ፊንፊኔ ቅዳሜ መስከረም 24 በአዲስአበባ ፤ እንዲሁም ሆረ ሀርሰዴ በማግስቱ መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም በቢሾፍቱ ”ኢሬቻ ለሀገር ማንሠራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል።
በደሳለኝ ሙሐመድ