በትምህርት ስርአት ውስጥ ያጋጠመውን ስብራት ለመጠገን ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዘላላም ሙላቱ (ዶ/ር) ተናገሩ።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም አካል የሆነውን የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን በጫወታ የማስተማር ስነ ዘዴን ለማገዝ ለ21 ትምህርት ቤቶች አጋዥ ግብአቶችን አስረክቧል።

በግብአት ርክክብ ስነ-ስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዘላላም ሙላቱ (ዶ/ር)፤ የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን በጫወታ መር የማስተማር ስነ-ዘዴ የተማሪዎችን ትምህርት የመቀበል አቅም ውጤታማ እያደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል።
በትምህርት ስርአት ውስጥ ያጋጠመውን ስብራት ለመጠገን ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል።
በጨዋታ የማስተማር ስነ ዘዴን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻሻል ትምህርት ቢሮው ተከታታይነት ያለው የግብአት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት ሃላፊው፤ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም የሚደረጉ ድጋፎችን ለታለመት አላማ መጠቀም እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በወንድምአገኝ አበበ