የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት በርካቶችን እያሳተፈ በደምቀት መካሄዱን ቀጥሏል፡፡
በትናንትናዉ ዕለት በተከፈተዉ የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት ላይ የክልሉ ፀጋዎች ለእይታ ቀርበዋል፡፡ የባህር ማዶ እና የሀገር ዉስጥ ጎብኝዎች በስፋት እየተሳተፉ ነዉ፡፡
ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉ የቱሪዝም ሳምንቱ ተሳታፊዎች እና ጎብኝዎች የቱሪዝም ሳምንቱ የኦሮሚያን ብሎም የሀገርን ፀጋ በዉል የተረዳንበት ነዉ ብለዋል፡፡
ሀገራዊ ፍቅር በህብረት እና መተሳሰብ ላይ መሰረቱን የጣለ አብሮነትን እዉን ከማድረግ አንፃር ሳምንቱ ሚናዉ የላቀ ስለመሆኑም ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡
በቱሪዝም ሳምንቱ ላይ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትም እየተሳተፉ ነዉ፡፡
በተመስገን ይመር