የመደመር መንግሥት መጽሀፍ የአስተሳሰብ ችግርን ማስተካከል ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን እንደሚያነሳ ምሁራን ተናገሩ

You are currently viewing የመደመር መንግሥት መጽሀፍ የአስተሳሰብ ችግርን ማስተካከል ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን እንደሚያነሳ ምሁራን ተናገሩ

AMN – መስከረም 22/2018 ዓ.ም

የመደመር መንግሥት መጽሀፍ የኢትዮጵያ መሠረታዊ ችግር የሆነውን የአስተሳሰብ ችግር ለማስተካከል የሠውን ጭንቅላት መገንባት ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን እንደሚያነሳ ምሁራን ተናግረዋል፡፡

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በመደመር በመንግስሥት መጽሃፍ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የፓናል ውይይት እያካሄዱ ነው።

በውይይቱ ሙሁራን በመጽሀፉ ጭብጥ ላይ እይታቸውን አጋርተዋል። መጽሀፉ አስተሳሰብን፣ ፍልስፍናን፣ ርዕዮተ ዓለምንና የኢትዮጵያን ቀጣይ እጣ ፈንታ መንገድ ጠቋሚ ስለመሆኑም በሙሁራኑ ተነስቷል።

ውድድር በሞላበትና ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም፣ኢትዮጵያ ያለችበትንና የደረሰችበትን ደረጃ በመጠየቅ ሀገር ለማሳደግና ከድህነት ለመውጣት ችግሮችን ማለየትና መፍትሄን ማሳየት በጸሀፊው በቁጭት መታየቱንም ተናግረዋል። ባለፉት ዘመናት በነበሩ መሪዎች የተስተዋሉ ድክመቶችንና ጥንካሬዎችንም በመዳሰስ ለምን ወደ ኋላ ቀረን በማለት “የኤሊ ጉዞ” የሚል ምሳሌ ጸሀፊው ዳሰዋል።

ለእነዚህ የኢትዮጵያ መሠረታዊ ችግሮች የአስተሳሰብ ችግሮች በመሆናቸው የሠውን ጭንቅላት መገንባት ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ፀሀፈው በመፅሀፉ አመልክተዋል ሲሉ ሙሁራኑ አመልክተዋል። ሌሎች ሀገራትም እንደ ኢትዮጵያ ማደግ ለሚፈልጉ አስፈላጊ እሳቤን ያካተተ ስለመሆኑ ነው ሙሁራኑ ያመላከቱት።

መጽሀፉ የማህበራዊ እና የፖለቲካ ስብራትን ያሳየ ከመሆኑም በተጨማሪ በከተማ ልማት፣ በቱሪዝም፣ በሰው ልማትና በሌሎችም ጉዳዮች ላጋጠሙ ችግሮች መንስኤና መፍትሄዎች ተዳሰዋል ብለዋል። ሙሁራኑ አክለውም፣ መጽሀፉ የወደፊቱን ይተልማል፤ ያለውንም ይጠብቃል ብልዋል፡፡

ለቀጣዩ የኢትዮጵያ መፍትሄ መደመርና ሁሉም ባህሉን፣ ወጉንና እሴቱን በማክበር፣ ለእድገት መነሳት እንደሚገባም መንገድ ያሳየ ስለመሆኑም ተነስቷል። በመደመር መንግሥት መጽሀፍ ፖናል ውይይት ላይ ሙሁራን፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review