መሬ ሆ ……………….

You are currently viewing መሬ ሆ ……………….

AMN – መስከረም 23/2018 ዓ.ም

እናቶች እና አባቶች ለምለም ሳር እና አበባ ይዘው

‎መሬ ሆ ……

ጉድቻ መርጋ ቶሌ

ሆያ ያ መሬ ሆ…..

ጉራቻ ገራን ቡሌ

ሆ ያ መሬ ሆ

መሬ ሆ ……..

ኡርጋን ኬ ፎሊ ኬ

ሆ ያ መሬ ሆ…..

መሬ ሆ ..እያሉ ጭጋጉ መገፈፉን: ፈጣሪያቸው ምህረት ማድረጉን ከዘመን ዘመን ማሸጋገሩን ይገልፃሉ በዕለተ ኢሬቻ ።

የልምላሜ ዘመን መምጣቱን በዜማቸው ያበስራሉ ።

የኦሮሞ እናቶች ወይም ሀዳ ስንቄዎች ከረጅም ዘመናት ጀምሮ ሜዳ ሸንተረሩን በልምላሜ ላጎናፀፈው አምላካቸው እያዜሙ የሚያመሰግኑበት ሥርዓት ነው ኢሬቻ ።

በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ኢሬቻ የብሩህ ዘመን አብሳሪ መሆኑ በጽኑ ይታመናል። ።

ለዚህ ነው የበአሉ ታዳሚዎች በኢሬቻ በዓል ወቅት አበባ እና ቄጤማ በእጃቸው ይዘው ይህንን ለምለም ሳር እና አበባ ላበቀለው አምላካቸው ምስጋና የሚያቀርቡት።

የኢሬቻ በዓልን ከሚያደምቁ ባህላዊ አልባሳት በተጨማሪ በእናቶች እና በአባቶች የሚዜሙ ጥዑመ ዜማዎች ተጠቃሾች ናቸው ።

ይህንን አስመልክቶ ኤ ኤም ኤን ዲጂታል ድምፃዊ በሻዳ ነገዎ ጋር ቆይታ አድርጓል።

በአፋን ኦሮሞ ከመዝፈን በተጨማሪ ግጥም እና ዜማ እንደሚደርስም ይገልፃል።

በኢሬቻ በዓል ወቅት አባ ገዳዎች እና እናቶች ወደ መልካ ሲሄዱ መሬ ሆ …….. ደርሰን መጣን እያሉ እንደሚያዜሙ ድምፃዊ በሻዳ ያስረዳል።

አባ ገዳዎች እንደየመጡበት ባህል እና ወጉን በጠበቀ መንገድ የአባገዳዎችን ወይም የሀዳ ሲንቄዎችን ዜማ እየተቀበሉ እና እያጀቡ ዕለቱን ያከብራሉ ሲልም ያብራራል።

ሀዳ ሲንቄዎች በኢሬቻ ቀን የሚያዜሙት ዜማ ደግሞ ………..

‎ኢሬቻ አና ዱፉ

‎ኖሩ ያ መልካ አራረኬ

‎ኢሬቻ አና ዱፉ

‎ኖሩ ያ ቱሉ አራረኬ ………………. እያሉ በዜማቸው ለእርቅ መምጣታቸውን እንደሚገልጹም ያስረዳል።

ይህም ዜማ ኢሬቻ ትልቁ ትርጉሙ የእርቅ እና ይቅር የመባባል ወቅት በመሆኑ ነው በማለት ድምፃዊው ተናግረዋል።

ድምፃዊ ዝናሽ ሎሌ በጉጂ ኦሮሞ ሙዚቃ ከሚታወቁ ድምፃውያን መካከል አንዷ ናት።

በተለያዩ ባህላዊ አልባሳቶች በዓሉ ከመድመቁ በተጨማሪ አባ ገዳዎች እና ሀዳ ሲንቄዎች ወደ መልካ ሲሄዱ መሬ ሆ……… እንዲሁም ኢሬቻ አና ዱፉ …… እያሉ እንደሚያዜሙ ተናግራለች።

ከዚህ በተጨማሪ ወጣቶች እና ታዳጊዎች ደግሞ እንደየመጡበት ባህል እና ወግ የተለያዩ ዜማዎችን ያዜማሉ።

በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review