የሆረ ሃርሰዴ የኢሬቻ በዓል በመልካ ሆረ ሀርሰዴ ‘ኢሬፈና’ ምስጋና የማቅረብ ሥነ-ሥርዓት በማከናወን ተከበረ

You are currently viewing የሆረ ሃርሰዴ የኢሬቻ በዓል በመልካ ሆረ ሀርሰዴ ‘ኢሬፈና’ ምስጋና የማቅረብ ሥነ-ሥርዓት በማከናወን ተከበረ

AMN – መስከረም 25/2018 ዓ/ም

በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ‘ኢሬፈና’ ወይንም ምስጋና የማቅረብ ሥነ ሥርዓት በማከናወን በድምቀት ተከብሯል።

በዓሉ አባ ገዳዎች፤ ሃደ ሲንቄዎች፤ ቄሮዎች፤ ቀሬዎች፤ ፎሌዎች፤ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች፤ ብሄር ብሄረሰቦች፤ የሃገር ዉስጥና የዉጭ ሃገራት ቱሪስቶች በተገኙበት ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል፡፡

የበዓሉ ታዳሚዎች “ሆ ያ መሬ ሆ …” እያሉ አስቸጋሪዉን የክረምት ወራት አሳልፎ ለጸደይ /ብራ/ ላደረሳቸዉ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ምስጋና በማቅረብ ከዘመን ዘመን መሸጋገራቸውን ያበሰሩ ሲሆን ስለመጪዉ ጊዜም ተስፋና መልካም እድልን ተመኝተዋል፡፡

የእርቅ፣ የሠላምና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነው ኢሬቻ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ከማጠናከር ባለፈ ለቱሪዝም ዘርፉ እድገት ጉልህ ድርሻ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አለማየሁ አሠፋ ከተማዋ ቀደም ሲል ከነበራት ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ መስህብ ላይ አሁን ላይ የተሠራው የኮሪደር ልማት ተጨማሪ መስህብ መፍጠሩን በአሉን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ” ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት ” በሚል መሪ ቃል በሆረ ሃርሰዴ በደማቅ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በበረከት ጌታቸዉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review