ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ የተዘረጉ የመሰረተ ልማት አውታሮችን የሰረቁ እና የተሰረቀውን ንብረት የገዛን ግለሰብ ይዞ ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ

You are currently viewing ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ የተዘረጉ የመሰረተ ልማት አውታሮችን የሰረቁ እና የተሰረቀውን ንብረት የገዛን ግለሰብ ይዞ ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ

AMN – መስከረም 26/2018 ዓ.ም

ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ የተዘረጉ የመሰረተ ልማት አውታሮችን የሰረቁ እና የተሰረቀውን ንብረት የገዛን ግለሰብ ይዞ ምርመራ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

መምያው ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ፤ መኩሪያ መዐዛ እና ተክላይ ደሳለኝ የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረደ 11 ልዩ ቦታው ICT ፓርክ አካባቢ መስከረም 6 ቀን 2018 ዓ/ም በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ ለህዝብ ግልጋሎ እንዲሰጥ በኮሪደር ልማት የለማን የኤሌክትሪክ ኬብል በመቁረጥ ይዘው ሊሰወሩ ሲሞክሩ በወቅቱ በወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሰፈራ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አባላት እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡

ፖሊስ በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ባደረገው ተጨማሪ የምርመራ ማስፋት ስራ ግለሰቦቹ በተደጋጋሚ ጊዜ ወንጀሉን ሲፈፅሙ ማረጋገጡንና የተሰረቁ ኬብሎችን ሲቀበል የነበረውን ተገኝ ገበየሁ የተባለውንም የሌባ ተቀባይ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ለህዝብ ጥቅም የተገነቡ የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ እየደረሰ ያለውን የስርቆት ወንጀል ለመከላከል የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ለሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶች መበራከት የሌባ ተቀባዬች አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ በየአካባቢው የሚገኙ የሌባ ተቀባዬችን አጋልጦ በመስጠት ለፖሊስ የወንጀል መከላከል ሥራ ድጋፉን ሊያጠናክር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review