መድሃኒቶችንና የህክምና መሣሪያዎችን በሀገር ውስጥ በማምረት ከፍተኛ ውጤት መገኘቱ ተገለፀ

You are currently viewing መድሃኒቶችንና የህክምና መሣሪያዎችን በሀገር ውስጥ በማምረት ከፍተኛ ውጤት መገኘቱ ተገለፀ
  • Post category:ጤና

AMN – መስከረም 26/2018 ዓ.ም

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ኘሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የ2ዐ17 በጀት አመትን አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫ አቅርበዋል፡፡

በዚሁ ጊዜ መንግስት በጤና ዘርፍ ባለፉት አመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን መነሻ በማድረግ ክፍተቶችን የመሙላት ስራ ሰርቷል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በተሰራው ሥራም በሽታ ከመከላከል ባለፈ አክሞ በማዳን ላይ በልዩ ትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል፡፡

በጤናው ዘርፍ መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ከመስጠት ባሻገር መድሃኒቶች እና የህክምና መሣሪያዎችን በሀገር ውስጥ በማምረት ከፍተኛ ውጤት መገኘቱንም ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

በ-በረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review