ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጪ ንግድ 8.3 ቢሊዮን ዶላር አግኝታለች ሲሉ ኘሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪካዊ እጥፋት በማስመዝገብ ከወጪ ንግድ 8.3 ቢሊዮን ዶላር አጊንታለች ያሉት ኘሬዝዳንቱ፣ ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር 115.8 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን አመላክተዋል።
በሲሚንቶ ምርት በ2016 በጀት ዓመት 7.5 ሚሊዮን ቶን መገኘቱንን እና ይህም በ2017 በጀት አመት 9.1 ሚሊዮን ቶን መገኘቱን ተናግረዋል።
ከ150 በላይ አለም አቀፍ ኮንፈረንሶች በሃገሪቱ መካሄዳቸውን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ የዲጅታል ኢኮኖሚ አመላካቾች በከፍተኛ ሁኔታ እድገት አሳይተዋል፡፡
የባንክ ብድር የመስጠት አቅም በማደጉ 822.8 ቢሊዮን ብር ብድር መለቀቁን እና ከዚህ ውስጥ 77 በመቶ ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።
በ- ሔለን ተስፋዬ