Pulse of Africa የአፍሪካን ድምፆች የሚያጎላ፣ ቀጠናዊ ትስስርን የሚያጠናክር እና አኅጉራዊ ስኬቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና ሕልሞችን በአፍሪካዊ እይታ የሚገልጥ ሚዲያ የመሆን አላማ እንዳለዉ ተገለጸ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ Pulse of Africa የተሰኘ የፓን አፍሪካ ሚዲያ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተዋል።
ሚዲያው ጠቅላይ ሚኒስትር እኤአ በ2022 በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የአፍሪካን እይታ እና ትርክት የሚያንፀባርቅ የአኅጉራዊ ሚዲያን አስፈላጊነት አስመልክተው ያቀረቡትን ጥሪ በመመርኮዝ የተመሠረተ ነው።

Pulse of Africa የአፍሪካን ድምፆች የሚያጎላ፣ ቀጠናዊ ትስስርን የሚያጠናክር እና አኅጉራዊ ስኬቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና ሕልሞችን በአፍሪካዊ እይታ የሚገልጥ ሚዲያ የመሆን አላማ እንዳለዉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡