የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር 20ኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል አከባበርን በተመለከተ ከበዓሉ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ተቋማት እና የክፍለ ከተማ አፈጉባዔዎች ጋር ተወያይተዋል።
የበአል አከባበሩን በተመለከተ የተዘጋጀ መሪ ዕቅድ የአፈጉባኤ ልዩ ፅ/ቤት ሓላፊ አቶ መንግስቱ ላማሮ ያቀረቡ ሲሆን በዓሉ በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መካከል በብዝኃነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ሥር እንዲሰድ እና እንዲዳብር በማድረግ ህብረ ብሔራዊ አገራዊ አንድነትን የሚያጎለብት መሆኑን አብራርተዋል።
የውይይት መድረኩን የመሩት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ሀገራዊ በዓሉ በፌደሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና ሆሳዕና ከተማ የሚከበር መሆኑን ገልፀው በአዲስ አበባ ከተማ የበዓል አከባበሩ በምክር ቤት አስተባባሪነትና በቁልፍ የባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ የሚፈጸም መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።
የዘንድሮው በዓል በተለያዩ መመዘኛዎች ልዩ እንደሚሆን የገለፁት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና በተደራጀ አቅም እና የሕዝቦች አንድነትን በማጠናከር፣ አብሮነትን እና ዴሞክራሲን በማጎልበት ረገድ በዓሉ ሚናው የላቀ መሆኑን ማስረዳታቸዉን ከከተማዉ ምክር ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡