በአፍሪካ ዞን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አንድ የተደለደለችው ኢትዮጵያ ዘጠነኛ ጨዋታዋን ዛሬ ታደርጋለች፡፡ ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ እንደማታልፍ ቀድማ ያወቀችው ኢትዮጵያ ጊኒ ቢሳውን ትገጥማለች፡፡
ዋልያዎቹ ቀደም ብለው ባደረጓቸው ስምንት የማጣሪያ ጨዋታዎች ጅቡቲን ብቻ አሸንፈዋል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ከአንዱ ድል ውጪ ሦስት ጨዋታዎችን አቻ በመውጣት በስድስት ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በስምንቱ ጨዋታዎች ሰባት ግብ ከመረብ ሲያሳርፍ 11 ግቦች ደግሞ ተቆጥረውበታል፡፡
ኢትዮጵያ በሜዳዋ ማድረግ የነበረባት የዛሬውን ጨዋታ በሩዋንዳ አማሆሮ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ ታከናውናለች፡፡
በዚሁ ምድብ አንድ ወደ ዓለም ዋንጫው ለማለፍ አንድ ነጥብ ማግኘት የሚበቃት ግብፅ ጅቡቲን ስትገጥም ሴራሊዮን ከ ቡርኪና ፋሶ ትጫወታለች፡፡ ሁለቱም ጨዋታዎች ምሽት 1 ሰዓት ላይ ይጀምራሉ፡፡
በሸዋንግዛው ግርማ