ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት ጊዜያት በመዲናዋ የተከናወኑ ከተማዊ ፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች በተሳካ መልኩ በድምቀት እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመሰገኑ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት ጊዜያት በመዲናዋ የተከናወኑ ከተማዊ ፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች በተሳካ መልኩ በድምቀት እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመሰገኑ

AMN መስከረም 28/2018

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት ጊዜያት በመዲናዋ የተከናወኑ ከተማዊ ፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች በተሳካ መልኩ በድምቀት እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመሰገኑ፡፡

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በአዲስ አበባ በድምቀት ተከብረዋል፡፡

በተጨማሪም ከ25 ሺህ በላይ አለም አቀፍ ተሳታፊዎች በተሳተፉበት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እና የአፍሪካ ካረቢያን ሀገራት መሪዎች ጉባኤ በስኬት ተጠናቀዋል።

እንዲሁም ባለፉት ጊዜያት በቅደም ተከተል የተከናወኑ የአለም ፣ የአህጉር እና የሀገር አቀፍኩነቶች፣ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ፕሮግራሞች ለአብነትም የአየር ንብረት ለዉጥ ጉባኤ፣ መስከረም አንድ በመስቀል አደባባይ የተከናወነው የወንጌል አማኞች የአምልኮ ፕሮግራም ፣ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተካሄዱ ህዝባዊ ሰልፎች ፣የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ ክብረ በዓላት እጅግ ወንድማማችነት ፣ እህትማማችነት በሰፈነበት መንፈስ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር መከበሩ የህዝባችንን ጨዋነት ዳግም ያረጋገጠ ነዉ ብለዋል።

ሁሉንም ሃገር አቀፍና አለማቀፍ ጉባኤዎች እንዲህም ሃይማኖታዊ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ በየደረጃዉ ያለ አመራር ፣ የሆቴል ባለቤቶች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ፣ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርት አምራቾችን የዋጋ ንረትና የምርት እጥረት እንዳይኖር በማድረጋቸዉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አመስግነዋል።

በተለይም የሀይማኖት አባቶች ፣ አባ ገዳዎች ፣ ሀደ ስንቄዎች ክብረ በዓላቱ እሴታቸዉን ጠብቀዉ እንዲከበሩ በማስተባበር ረገድ ለነበራቸዉ የላቀ አስተዋፆ ምስጋና አቅርበዋል ።

የፌደራል ፣ የአዲስ አበባ እና የሸገር ከተማ የፀጥታ አካላት እና አመራሮችንም አመስግነዋል ።

አለም አቀፍ ጉባኤዎቹ ፣ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፎቹ ፣ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ክብረ በዓላቱ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር መከበራቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ኩነቶቹ ለነዋሪዉ ህዝባችን የገቢ ምንጭ በመሆን በከተማችን ኢኮኖሚ ላይ አይነተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንም ከንቲባ አዳነች ትላንት ማምሻዉን በተካሄደዉ የምስጋና ፕሮግራም ላይ አክለው መግለጻቸዉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review