ዕውቅናውን ያበረከተው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ነው ፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጉባኤው የሚያከናውናቸውን ስራዎች ከህዝብ ዘንድ በማድረስ ከፍተኛ አበርክቶ የነበረው ሲሆን የተለያዩ ሃይማኖታዊ በአላትን በቀጥታ ስርጭት በጥራት ሲያደርስ ቆይቷል ። በተጨማሪም የዜና ሽፋኖችን በመስጠት ኃላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱ ተገልጿል ።
በመሆኑም የሚዲያ ተቋሙ በሰራው ስራ የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የትውልድ ድምጽ ለሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዕውቅና አበርክቶለታል ።
እውቅናውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ተረክበዋል።
በ-ሃብታሙ ሙለታ